አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለሚያስገነባው የቢሾፍቱ ባቡር አካዳሚ መሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በመርሐ ግብሩ ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸውን (ኢ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሚኒስቴሩ በባቡር መሰረተ ልማት ክልሎችን በማስተሳሰር የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ፍላጎት ለማሳለጥ እየሰራ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት መሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የባቡር አካዳሚ ከውጭ የሚገቡ ባለሙያዎችን በመቀነስ ኢትዮጵያ በቀጣናው ማዕከል እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል።
ይህም ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በዓለም ገበያ ውስጥ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ ለኢትዮጵያም የውጭ ምንዛሪ ማግኛ እንደሚሆን አመላክተዋል።
ህሊና በላቸው (ኢ/ር) በበኩላቸው የአፍሪካን የባቡር ትራንስፖርት በዕውቀት ለመደገፍ ማዕከሉ አስተዋፅኦ እንዳለው አንስተው÷ አካዳሚው ለትውልድ ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ብልፅግና መሰረት ነው ብለዋል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ የአካዳሚው መገንባት የቱሪስት መዳረሻ ለሆነችው ቢሾፍቱ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
በፍቅርተ ከበደ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

