አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው አሉ፡፡
በዛሬው ዕለት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በፍጥነትና በጥራት በ24 ህንፃዎች የተገነቡ 1 ሺህ 287 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ተመርቀዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት የማህበረሰባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወንን ነው ብለዋል።
የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ380 ሺህ በላይ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል ያሉት ከንቲባዋ÷ ይህም ከለውጡ በፊት ባሉት 17 ዓመታት ከተገነቡት 179 ሺህ ቤቶች የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
የመፍጠርና የመፍጠን መርህን በተጨባጭ ካረጋገጥንባቸው ፕሮጀክቶች ይህ ትልቅ ስኬት 24/7 የሥራ ባህልን በተግባር ላይ በማዋል የተገኘ ውጤት ነውም ብለዋል።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ የሚገኙ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ዛሬ የተመረቁ ከ11 እስከ 18 ወለል ያላቸው 24 ሕንፃዎች የያዙት የመኖሪያ ቤቶችን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ጭምር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
በዚህም የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን፣ የስፖርት ሜዳን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን እና ሌሎች የጋራ መገልገያዎችን አሟልተዋልም ነው ያሉት።
ፕሮጀክቱ ከግንባታ ባለፈ በርካታ የሥራ ዕድሎችን እና የእውቀት ሽግግርን ለወጣቶች ማስገኘቱን ጠቅሰው÷ ጥራትንና ፍጥነትን በተመሳሳይ ጊዜ ማረጋገጥ እንደምንችል አሳይቷል ብለዋል።
ቤቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለንግድ ባንክ ሰራተኞች ያስረከብን በመሆኑ በአንድ በኩል የቤት እጥረትን ለመፍታት አማራጭ ርምጃ ያስቀመጠ ሲሆን÷ በሌላ በኩል የቤት ልማት ፈንድን የፈጠረ ጭምር ነው ሲሉም አስረድተዋል።
ለዚህ ሥራ ስኬት የበኩላቸውን ለተወጡ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ተቋማት ከንቲባዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

