አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባቡር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ አቅም ይሰጣል አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ጋር በመተባበር ከሚዲያ ተቋማት ባለሙያዎችና ከማሕበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር በቤኑና መንደር ጉብኝት እያካሄደ ሲሆን÷ የባቡር ትራንስፖርትን ለቱሪዝም ያለው ሚና በሚል ሐሳብ የባቡር ቱሪዝም ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
ሚኒስትር ዴዔታው ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ከኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ጸጋዎች የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ነው፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ለቱሪዝም ዘርፍ ያለው አበርክቶ ተቋማዊ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ ቱሪዝምን ያለትራንስፖርት ማሰብ አይቻልም ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የባቡር ትራንስፖርትን በአግባቡ እየተጠቀምን አልነበረም ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው÷ ባቡርን ከቱሪዝም ጋር በማቀናጀት አማራጭ፣ ፈጣን እና ምቹ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የተለያዩ ክልሎችና የቱሪስት መዳረሻዎችን እንደሚያካልል ጠቅሰው÷ ይህም ለቱሪዝም ከፍተኛ አቅም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ የባቡር ቱሪዝምን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችን የማልማት ስራዎች ይከናወናሉም ነው ያሉት፡፡
የዛሬው ጉዞ በአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን አንስተው÷ ባቡር በራሱ የቱሪዝም ስበት ማዕከል እንደሆነ እና የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

