አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች አደረጃጀቶች የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ።
ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ኮሚሽኑ ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
በዚህ ሒደትም ሴቶች ፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
የኮሚሽኑ ዓላማና ተግባር ላይ ዜጎች በቂና ግልጽ ግንዛቤ እንዲያገኙና ለምክክሩ ውጤታማነት የድርሻቸውን እንዲወጡ የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን አመልክተዋል፡፡
ከተቋማት፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከዳያስፖራውና ከሌሎችም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አጀንዳ መሰብሰቡንም አንስተዋል።

