Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓለም አቀፍ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በዓለም ለ34ኛ ጊዜ ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው።

ዓለም አቀፍ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን ወይም ነጭ ሪቫን ቀን “ጥቃትን የማይታገስ ማሕበረሰብ ለትውልድ ግንባታ “በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በኢትዮጵያ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘው የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በተለያዩ ንቅናቄዎች ለተከታታይ 16 ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የሲቪል ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሙና አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጾታዊ ጥቃት ሴቶችና ሕጻናት በየዘርፉ በሚካሄዱ የልማት ሥራዎች ውስጥ እንዳይሳተፉ ያደርጋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የጤና፣ ሥነ ልቦና እና ሌሎች ጠባሳዎችን ጥሎ እንደሚያልፍ ጠቁመው ÷ ድርጊቱን በጋራ ልንከላከለውና ልናወግዘው ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ጾታዊ ጥቃት የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሴቶችና ሕጻናት ሰብዓዊ መብት መከበር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

አዳዲስ የአሰራርና የአደረጃጀት ለውጦችን ለማካሄድ፣ የተቋማትን አቅም ለማጠናከር እንዲሁም የተቀረጹ የሕግ ማዕቀፎችን ለመተግበር ጠንካራ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጾታዊ ጥቃትን የመከላከል እና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በማስቆም እና በመከላከል ረገድ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሶስና አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version