አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በጋራ ያዘጋጁት 5ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን ማሰልጠኛው ተቋማት ማህበር ጉባኤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች፣ የአቪየሺን ዘርፍ ኃላፊዎችና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አበራ በአቪዬሽን ዘርፉ ለሚስተዋሉ ችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማፈላለግ እና ልምዶችን ለመለዋወጥ ጉባኤው ጠቃሚ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን አካዳሚ በ50 ዓመታት ቆይታው የአጭር እና የረዥም ጊዜ የማጠናከሪያ ስራዎችን በመስጠት ለዘርፉ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ መቀጠሉን አስረድተዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው፤ የአቪዬሽን ዘርፉ ወደተለያዩ ዘርፎች የሚሻገር ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶበታል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ ጉባኤ በአፍሪካ በዘርፉ የሚስተዋሉ ውጤታማ ጅምሮችን ማጠናከር እና የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ውይይት ይካሄዳል።
እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን የሚዳስስ የፓናል ውይይትና ሲምፖዚየምም ተዘጋጅቷል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

