Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ጉዞ ውስጥ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል – አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ጉዞ ውስጥ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል አሉ፡፡

በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክትን በተመለከተ ገለጻ ቀርቧል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቴክኖሎጂ፣ በዲዛይን እና ወደር በሌለው ትስስር የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን መዲና እንድትሆን አድርጓታል፡፡

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የአቪዬሽን መግቢያ በር የመሆን አቅምን እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህም በአፍሪካ ትልቁ አየር ማረፊያ እንዲሆን አድርጎታል።

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለወደፊት ንግድ፣ ጉዞ እና አህጉራዊ ትስስር ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ነው የተገለጸው፡፡

ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከአየር ማረፊያ በላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና ለአህጉራዊ ውህደት በመላው አፍሪካ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሥራ ከጀመረ በኋላ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያለውን ጫና በመቀነስ ኢትዮጵያና አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሻለ ሁኔታ እንዲገናኙ ያስችላል።

የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው በሚሠራበት ወቅት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ልማትን እንደሚደግፍ ተገልጿል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version