አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በማጠቃለያ መድረኩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር መፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል።
መርሐ ግብሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፥ በመርሐ ግብሩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከ510 በላይ ከተሞች እንዲሁም ከ80 በላይ አጋር ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንቱ ባከናወነቻቸው ከ11 ሺህ በላይ ሁነቶች በዓለም 1ኛ ደረጃን መያዝ እንደቻለች ተገልጿል፡፡
የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መድረኩ በጋራ እንገንባ የሚለውን መሪ ሀሳብ በመተግበር በጋራ የት መድረስ እንደሚቻል የታየበት ነው፡፡
ይህንን ለማስቀጠል ከመንግሥት እስከ ታች ድረስ ሁሉም በጋራ ሊረባረብ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በማጠቃለያ መድረኩ ኢንተርፕረነሮች ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ይከናወናል።
በሶስና አለማየሁ

