Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሆንግ ኮንግ 128 ሰዎችን ለሕልፈት የዳረገው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሆንግ ኮንግ በጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 128 ደርሷል አሉ የአካባቢው ባለስልጣናት፡፡

ባሳለፍነው ረቡዕ ዕለት በተከሰተው የእሳት አደጋ ለሕልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ ከ200 በላይ ሰዎች እስካሁን ያሉበት አልታወቀም፡፡

ከ4 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በሚኖሩባቸው የጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች የተከሰተውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የሆንግ ኮንግ የደህንነት ኃላፊ ክሪስ ታንግ ገልጸዋል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠር ከ2 ሺህ በላይ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ÷ በአደጋው ምክንያት በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ሰዎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ኃላፊው በሰጡት መግለጫ በሁሉም ሕንጻዎች ላይ የተገጠሙ የእሳት አደጋ የጥንቃቄ መልዕክት መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበር አመልክተዋል፡፡

የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ፖሊስ በይፋ ምርመራ መጀመሩንና መረጃዎችን እያሰባሰበ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

Exit mobile version