Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ  አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

በዚህ መሰረት፦

1ኛ. ሁሉንም የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለከተማው ነዋሪ ተደራሽ ለማድረግ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ አነስተኛ ክፍያ ተመን እና በነፃ መጠቀም የሚቻልበት አሰራር ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

2ኛ. የጤና ተቋማት የሥራ አማካሪ ቦርድ ማቋቋሚያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

3ኛ. በመንግስት እና የግል አጋርነት የሚተዳዳሩ ሆስፒታሎች የቦርድ የውስጥ አሰራር ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

4ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማስተላለፉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version