Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሐረሪ ክልል የቱሪዝም መስህቦችን ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ ማድረግ ተችሏል – ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የቱሪዝም መስህቦችን መልሶ በማልማትና ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ በማድረግ ረገድ አበረታች ተግባር ተከናውኗል አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ።

መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የዓለም ቅርስ የሆነችውን ሐረር ከተማ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ በክልሉ የቱሪዝም መስህቦች በመልሶ ማልማት ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ እንዲሆኑ ተደርጓል።

በተለይም የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ላይ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ የተከናወነው የመልሶ ልማትና እንክብካቤ ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ምቹ በሆነው የሐረር ኢኮ ፓርክ አስደሳች የጅብ ትርኢት መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ሰው እና ጅብ በአንድ ላይ ተላምደው እንዲህ በአንድነት በትርዒት መልክ ማየት ግርምት የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው፤ ትርዒቱ ለቱሪዝም ዕድገት አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል።

ፓርኩ ሀገሪቱ ብሎም ከተማዋ ተመራጭ የቱሪስቶች መዳረሻ እንድትሆን ያስችላል ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version