ለአንድ ወር በኮምቦልቻ፣ ደሴና አካባቢው በከፊል ተቋርጦ የቆየው ኃይል ወደ አገልግሎት ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለአንድ ወር በኮምቦልቻ፣ ደሴና አካባቢው በከፊል ተቋርጦ የቆየው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት ተመልሷል።
አገልግሎቱ የተቋረጠው በኮምቦልቻ አንድ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ካሉት ሁለት ትራንስፎርመሮች መካከል በአንደኛው ላይ ባጋጠመ ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
40 ሜጋ ቮልት አምፒር ኃይል የመጫን አቅም ባለው ትራንስፎርመር ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ምክንያት በአካባቢው በከፊል ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱንም ገልጿል፡፡
በዚህም በትራንስፎርመሩ ላይ በደረሰው ጉዳት በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢያቸው ለአንድ ወር ያህል በከፊል ኃይል ተቋርጦ መቆየቱን አመላክቷል፡፡
ጉዳት የደረሰበትን ትራንስፎርመር ጠግኖ ዳግም አገልግሎት ለማስጀመር ከሪጅኑና ከማዕከል የተውጣጡ የጥገና ባለሙያዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተቋሙ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ተቋርጦ የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ በጥገና ሥራው ላይ ርብርብ ሲያደርጉ ለነበሩ ባለሙያዎች ምስጋና ቀርቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

