አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተገማች፣ ግልፅና ምቹ የካፒታል ገበያ ምህዳር መፍጠር አስችሏል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)።
ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል እየተካሄደ ነው።
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እንደ ጀማሪ ሳይሆን እንደ ነባር ተቋም በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
የካፒታል ገበያ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለግሉ ዘርፍ የጎላ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸው÷ በዚህም የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በተግባር የተገለጠ ውጤታማ ስራዎችን በብቃት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ገበያ መር የካፒታል ገበያ ዕድገት ለማምጣት የተመሰረተ መሆኑን አንስተው÷ በረጅም ጊዜ የግሉን ዘርፍ የፋይናንስ መሪ ለማድረግ የታለመ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተከናወነው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ተገማች ግልጽና ለገበያ ምቹ ምህዳር የፈጠረ መሆኑን በማንሳት÷ የባንኮችን የገንዘብ ክምችት ማሳደግና ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
ከዚህም ባለፈ ተወዳዳሪና ገበያ መር የፋይናንስ ስርዓት ማንበር የሚያስችል ምህዳር ተፈጥሯል ያሉት ያሎት ኢዮብ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ስርዓቱ መሳለጥ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ ብዝኃ የገበያ ስርዓትን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይኸውም ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ዕድገት አቀጣጣይ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች በማልት ጠቅሰው÷ ሪፎርሙ ምቹ የገበያ ምህዳር በመፍጠር ለኢትዮጵያ ብልጽግና የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተህልቁ በበኩላቸው÷ ባለስልጣኑ ህጋዊና ተቋማዊ ቅርፅ ይዞ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት የሚያዘምኑ በርካታ እንቅስቃሴዎች ማድረጉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ግቡን ለማሳካት ከቀጣናውና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠሩንም ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

