አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛኒያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
የታንዛኒያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዩጋንዳን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው የውድድሩ ሻምፒዮን የሆነው፡፡
ቀን 9 ሰዓት 30 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የታንዛኒያን የማሸነፊያ ግቦች ራዛኪ ምቤጌሌንዲ (2) እና ሉቅማን ምባላሳሉ አስቆጥረዋል፡፡
ዩጋንዳን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ደግሞ ቶማስ ኦጌማ እና ብሪያን ኦልዋ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ኬንያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወድድሩን በ3ኛነት አጠናቅቋል።

