አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል የሊጉን መሪነት ለማጠናከር ዛሬ ምሽት ብሬንትፎርድን በሜዳው ያስተናግዳል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ትናንት ምሽት ፉልሃምን 5 ለ 4 ማሸነፉን ተከትሎ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል፡፡
መድፈኞቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ለማድረግ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 በሚደረገው ጨዋታ ብሬንትፎርድን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በርስ ባደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል ሦስቱን ሲያሸንፍ፥ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በሌሎች የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች በፕሪሚየር ሊጉ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሊቨርፑል ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ሰንደርላንድን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ 5 ሰዓት ከ15 በሊጉ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ሊድስ ዩናይትድን የሚገጥም ሲሆን፥ ብራይተን ከአስቶን ቪላ፣ በርንሌይ ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ወልቭስ ከኖቲንግሃም ፎረስት ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

