አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ዛሬ ምሽት ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ይገናኛል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ ዌስትሃምን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ነጥቡን 24 በማድረስ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ዌስትሃም ዩናይትድ ሶስቱን በማሸነፍ የበላይነት ያለው ሲሆን፥ ማንቼስተር ዩናይትድ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡
ትናንት ምሽት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርሰናል ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን ያጠናከረ ሲሆን፥ ቼልሲ በሊድስ ዩናይትድ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
በአንፊልድ ሰንደርላንድን የገጠመው ሊቨርፑል 1 ለ 1 አቻ ሲለያይ፥ አስቶንቪላ ብራይተንን፣ ክሪስታል ፓላስ በርንሌይን እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ወልቭስን አሸንፈዋል፡፡

