አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የሙያ ማህበራት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ቀሪ ሥራዎች ውጤታማነት የበኩላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል አሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)።
ኮሚሽኑ ”የኢትዮጵያ የሙያ ማህበራት የላቀ ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኮሚሽኑ ምክክሩን አሳታፊና አካታች ለማድረግ ለተሳታፊ ልየታ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።
የሃይማኖት እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን፣ ማህበራትን፣ ታዋቂ ሰዎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መንግሥትንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተወካዮቻቸው በኩል ማሳተፍ መቻሉን ገልጸዋል።
በዚህም አብዛኛውን ሥራዎች ማከናወኑንና አሁን ላይ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ መድረሱን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔውን ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሁሉም ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለው አማራጭ ሀገራዊ ምክክር መሆኑን ገልጸው÷ ሁሉም አካል አጀንዳዎቹን ወደ ሀገራዊ ምክክሩ በማምጣት ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጀምሮ ከተለያዩ ማህበራት ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው÷ የኢትዮጵያ የሙያ ማህበራትም ለኮሚሽኑ ቀሪ ሥራዎች ውጤታማነት የበኩላቸውን ኃላፊነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
እስካሁን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ እንዲሳካ ላደረጉትና አሁንም እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

