አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መካከል ዘላቂ የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለክልሉ ህዝብ እፎይታን የሚፈጥር ነው አሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች።
አስተያየታቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሰጡት የከተማዋ ነዋሪዎች÷ እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው፤ በወንድማማቾች መካከል ያለው መገዳደል መቆም አለበት ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት የተቋረጠባቸው፣ አርሶና ነግዶ መብላትን ከባድ ያደረጉ ጊዜያት እንደነበሩ በማስታወስ÷ የክልሉ ነዋሪዎች ጦርነት አስከፊ በመሆኑ ይብቃ ልንል ይገባልም ነው ያሉት።
መንግሥት የሰላም አማራጭን በማቅረብና ጥሪ በማድረግ የሄደበት ርቀት የሚያስመሰግን እንደሆነ ገልጸው÷ ይህም ለመነጋገርና አብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይ መንግሥት የዘረጋው የሰላም መንገድ ለአማራ ክልል ህዝብ ትልቅ ፋይዳ ያለው እንደሆነም አስረድተዋል።
ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሱት ታጣቂዎችም በአማራ ክልል የነበረው ጦርነት በህዝቡ ላይ አሉታዊ ጫና እያስከተለ መሆኑን በመረዳት ወደ ሰላም መምጣታቸው የሚደገፍ ነው ብለዋል።
ሌሎችም ታጣቂዎች ወደ ሰላም አማራጭ መጥተው ችግሮችን በውይይት በመፍታት የአማራ ክልል ህዝብን የመልማት ጥያቄዎች እንዲመለሱ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።
መንግሥትም ለሰላም ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በኩል የተጀመረውን የሰላም ስምምነት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል በትናንትናው ዕለት ዘላቂ የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

