አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሽልማቱ የተበረከተላቸው በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ላይ ነው፡፡
በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያን ኢንፋቲኖ የወርቅ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡
ፊፋ ከወራት በፊት ለሰላም አስተዋፅኦ ያበረከቱ ግለሰቦችን እውቅና እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወሳል።
በዚህም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሽልማቱን በማሸነፍ የመጀመሪያው ሰው መሆን ችለዋል፡፡

