Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሲዳማ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 5 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 5 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር ደረሰ።

የባንኩ አክሲዮን ማኅበር የባለ አክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የሲዳማ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ማርሻለው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 5 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር በመድረስ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 111 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 1 ነጥብ 31 ቢሊየን መድረሱን ገልጸው÷ በበጀት ዓመቱ 126 ነጥብ 9 ሚሊየን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ጠቁመዋል።

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 3 ነጥብ 67 ቢሊየን ማድረስ ተችሏል ያሉት አቶ አብርሃም÷ አፈፃፀሙም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 200 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የባንኩ መጠባበቂያ ካፒታል ብር 77 ነጥብ 2 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን÷ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 31 በመቶ ዕድገት አለው ብለዋል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ለአዳዲስ እና ለነባር ደንበኞች 2 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር ብድር ማሰራጨቱንም አመላክተዋል።

በደብሪቱ በዛብህ

Exit mobile version