Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፈጠራን እና የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የቆየው ብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የማጠቃለያ መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ባለፉት 10 ቀናት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ሲካሄድ በቆየው ውድድር ማጠናቀቂያ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ኢንተርፕርነሮች፣ ተወዳዳሪዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘንድሮ ለ6ኛ ዙር የተካሄደው ውድድሩ ችግር ፈቺና ስራ ፈጣሪ የሆኑ ሃሳቦች ያፈለቁ ወጣቶች ሃሳባቸውን የሚያጎለብቱበትና ለውድድር አቅርበው ተሸላሚ የሚሆኑበት ሲሆን÷ አሸናፊዎቹ ሃሳቦቻቸውን ወደ ኩባንያ ማሸጋገር የሚችሉበት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ በዚህ ወቅት ኢንተርፕርነርሽፕ ለሀገር ግንባታ ምሰሶ መሆኑን ገልጸው÷ ውድድሩ ለሀገር የሚተርፉ ወጣቶች እንዳሉን የተረዳንበት ነው ብለዋል።

በቀጣይም ፈጠራን እና የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ብሎም ለማሳደግ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን በበኩላቸው÷ በዘንድሮው ውድድር 222 ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸውን ገልጸው÷ 100 ተወዳዳሪዎች አሸናፊ በመሆን ማጠናቀቃቸውን አመላክተዋል።

በብሩህ ኢትዮጵያ የፈጠራ ውድድር እስካሁን 1 ሺህ 350 የፈጠራ ሃሳቦች ተሸላሚ እንደሆኑና ከእነዚህ መካከልም 580 የሚሆኑት ወደ ኢንተርፕርነርሽፕ ተሸጋግረው ስታርትአፕ ላይ መሰማራቸው በመድረኩ ተገልጿል።

በሶስና አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version