Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኦሮሚያ ክልል 21ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ያዘጋጃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት ይከበራል።
21ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ጅማ ከተማ እንድታዘጋጀው በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ በሚገኘው 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ላይ መመረጧ ይፋ ተደርጓል።
በዚህም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የዝግጅቱን ሰንደቅ ዓላማ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ
Exit mobile version