Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ፍትሕን ለማስፈን በትኩረት መስራት ይገባል –  አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዘላቂ ፍትሕን ለማስፈን በትኩረት መስራት ይገባል አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ አዲስ ለተመረቁ የሚሊሻ አባላት በዛሬው ዕለት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀና የተሻለ ለማድረግ የልማት ሥራዎች በቁርጠኝነት እየተሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ከሌለ የልማት ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም ያሉት አቶ አርዲን ÷ በክልሉ የሰፈነውን ዘላቂ ሰላም  መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የመንግስት ትልቁ ሥራ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጠቁመው ÷ የታለመውን ግብ ለማሳካትም የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ፍትሕን ማስፈን ይገባል ነው ያሉት።

ከጸጥታ ሥራው ጎን ፍጥነትና ፈጠራ የታከለባቸው የሕዝቡን ኑሮ የሚቀይሩ የልማት ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎችን በማከናወን ብልጽግናን እውን ለማድረግም የሚሊሻ አባላት የሰላምና ልማት አርበኛ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አባላቱ ለዴሞክራሲና ፍትሕ መስፈን፣ ለሀሳብ ነጻነት መከበርና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version