Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕብረት ሥራ ማሕበራት ችግር ፈቺ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕብረት ሥራ ማሕበራትን በማዘመን ተወዳዳሪና ችግር ፈቺ እንዲሆኑ የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አምባዬ ወልዴ።

ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ በባሕር ዳር ከተማ ላለፉት 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።

ስልጠናው የሕብረት ሥራ የልማት አመቻች ሙያተኞችን አቅም በመገንባት ተቋማቱ ተወዳዳሪ፣ አትራፊና የማሕበረሰቡን የገበያ ክፍተቶች ከመሙላት በተጨማሪ በኢኮኖሚው ውስጥ ሁነኛ ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ያግዛል ተብሏል።

አቶ አምባዬ ወልዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሥልጠናው ባለሙያዎች የአዋጭነት ጥናቶችን በማጥናት የተቋማቱን አሠራር በቴክኖሎጂ ለማገዝ የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም ማሕበራቱ አባሎቻቸውን ከመጥቀም በላይ በኢኮኖሚው ውስጥ ድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት ሂደት የተጀመረው ለውጥ አንዲሳካ ከክልሉ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን ክትትልና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version