Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ 98 በመቶ ንግድ የሚከናወንበት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በትኩረት እየሰራች ነው አሉ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)።

“ኢትዮጵያን በንግድ በማስተሳሰር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር” የሚል መሪ ሐሳብ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ሂደትን የተመለከተ መድረክ ተካሂዷል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ለምታደርገው ድርድር 1 ሺህ 50 ጥያቄዎች ቀርበውላት ለሁሉም ምላሽ ሰጥታለች።

የዓለም የንግድ ድርጅት 96 በመቶ የዓለምን ሕዝብ ያቀፈና 166 አባል ሀገራት ያሉት በመሆኑ ኢትዮጵያም አባል ለመሆን በፈረንጆቹ የካቲት ወር 2003 ጥያቄ ማቅረቧን አስታውሰዋል።

የድርጅቱ አባል ለመሆን ረጅም ድርድርና ከአባል ሀገራቱ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ መስጠት እንደሚገባ አንስተው÷ በዚህም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ግንቦት 6፣ 2008 የመጀመሪያውን ድርድር አካሂዳለች ብለዋል።

በፈረንጆቹ ጥር ወር 2020 ላይ 4ኛውን ድርድር ዳግም በቁርጠኝነት ጀምራለች ያሉት ካሳሁን (ዶ/ር)÷ በ2025 መስከረም ወር ላይ ደግሞ 6ኛውን ድርድር ማከናወኗን አስረድተዋል።

ለአባልነቱ የባለብዙ ወገን ድርድር ከ56 ሀገራት ጋር መደረጉንና በሁለትዮሽ የሀገራት ድርድር ደግሞ ከቱርክ፣ አርጀንቲና እና ቻይና፣ ሩሲያ ጋር በጥሩ ሁኔታ ድርድር መካሄዱን አብራርተዋል።

በድርድሩ ሂደት ኢትዮጵያ 410 የህግ ማሻሻያዎችንና 32 ግዴታ የሚገባባቸው ውሎች መፈረሟን አመላክተዋል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version