Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ባህልና እሴት የተንጸባረቀበት መድረክ በሳዑዲ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሪያድ ሲዝን 2025 መርሐ ግብር ላይ ተሳትፋለች፡፡

በመርሐ ግብሩ የተገኙት በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) እንዳሉት÷የሪያድ ሲዝን 2025 ዓለም አቀፍ ዝግጅት ለኢትዮጵያ በርካታ ጠቀሜታዎችን የሚያስገኝ ነው።

የሪያድ ሲዝን ኢትዮጵያ ባህሏን እና ትውፊቶቿን ለዓለም በማሳየት አፍሪካን የምታስጠራበት ትልቅ አህጉር አቋራጭ ድልድይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መድረኩ የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና ባህላዊ አልባሳት ለዓለም ማሕበረሰብ የማስተዋወቅ እድል መፍጠሩን አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም በባህል፣ በሙዚቃ እና በልብስ አማካይነት የኢትዮጵያን ቱባ ታሪክና ልዩ ውበት በቀጥታ በማሳየት የቱሪዝም ፍሰትን ለመጨመር መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በዓለም አቀፍ ትዕይንቶች ላይ የተደርገው ተሳትፎ ኢትዮጵያ በጠንካራ አንድነት ስር አቅፋ የያዘቻቸውን ብዝሃነቶች ለማሳየት ያስቻለ ወርቃማ ዕድል እንደሆነም አምባሳደሩ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

መድረኩ በሳውዲ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያንና ዓለም አቀፍ ወዳጆች በአንድ ላይ በመሰባሰብ ባህላቸውን እንዲያከብሩና ማንነታቸውን እንዲያሳዩ ማስቻሉን ጠቁመዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version