አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ሕዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ቀን ከሌት እየሠራ ነው አሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፡፡
በአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እና የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ያደጉ ሀገራት የሕዝባቸውን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥተው በሚሠሩበት ዓለም ኢትዮጵያ ወደ ኋላ እንድትቀር የውስጥና የውጭ ጠላቶች እየሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።
መንግሥት እነዚህን ችግሮች ከመፍታት ጎን ለጎን ትላልቅ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የተጀመረውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥም መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ መመካከርና መወያየትን ባሕል በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡
ሉዓላዊነት የሚከበረው በጦርነት ብቻ ሳይሆን በምግብ ራስን በመቻል በመሆኑ ማሕበረሰቡ የሰላም ዘብ እንዲሆንም ጠይቀዋል።
አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው÷የግጭትና የድህነት ታሪካችን ፈተና ሁኖ እንዳይቀጥል ብልጽግና ፓርቲና መንግሥታችን ቀን ከሌት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
በሕዝባዊ ውይይቱ የባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ማሕበረሰብ ተወካዮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በደሳለኝ ቢራራ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

