አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ቀን 11:00 ላይ በክሪስታል ፓላስ ሜዳ ሴልኸርስት ፓርክ በሚደረገው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ወሳኝ ድል በማስመዝገብ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል።
በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ማንቼስተር ሲቲ 31 ነጥብ በመሰብሰብ ሁለተኛ ሲሆን፤ ክሪስታል ፓላስ ደግሞ በ26 ነጥብ አምስተኛ ላይ ተቀምጧል።
ትናንት ምሽት በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን ዎልቭስን 2 ለ 1 የረታው አርሰናል ነጥቡን 36 በማድረስ መሪቱን ማጠናከሩ ይታወቃል።
የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲካሄድ በተመሳሳይ 11:00 ሰንደርላንድ ከኒውካስል ዩናይትድ፣ ዌስትሃም ከአስቶንቪላ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከቶተንሃም ይገናኛሉ።
እንዲሁም ምሽት 1:30 ላይ ብሬንትፎርድ ሊድስ ዩናይትድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይካሄዳል።

