አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቁ ሥራዎች ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ የምክክር መድረክ ተጠናቅቋል።
ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የሕዝቦችን አንድነትና ትስስር እንዲሁም አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ኪነ ጥበብ ጉልህ ሚና አለው፡፡
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ትውልድን የመቅረጽ ኃላፊነት እንዳላባቸው ጠቁመው ÷ በተለይም ዜጎችን በሚያቀራርቡ ጉዳዮችና በብሔራዊ ጥቅም ላይ የጥበብን አቅም ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ብሔራዊ ጥቅም ከሚረጋገጥባቸው ጉዳዮች መካከል የቀይ ባሕር ጉዳይ አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ÷የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
መንግሥት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው ÷ለአብነትም መዋቅር ከመዘርጋት ጀምሮ ለጥበብ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
በጀማል አሕመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

