Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል አሉ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በ290 ሚሊየን ብር የተገነባው የጼጼ ዘመናዊ የዶሮ ማብዣና እርባታ ማዕከል በሚኒስትሩ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ፕሮጀክቱ ባለፉት ስድስት ዓመታት በተተገበረባቸው ሰባት ክልሎች ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በበኩላቸው መሰል ፕሮጀክቶች እንደ ሀገር እየተተገበረ የሚገኘውን የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር እንደሚደግፉ ገልጸው፥ የእንስሳት ሀብት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እንዳሉት፥ ማዕከሉ ለአካባቢው ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሰብ የተሻሻለ ዶሮ ዝርያን በተመጣጠነ ዋጋ በማቅረብ የስነ ምግብና የገቢ አቅማቸውን ማሻሻል ያስችላል፡፡

በተጨማሪም ለከተማው ማህበረሰብ የእንቁላልና የስጋ ዶሮን በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ባለፈ ለሀገሪቱ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል ነው ያሉት፡፡

ማዕከሉ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በቆላማ አካባቢዎች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው ፕሮጀክት አካል ሲሆን፥ በአንድ ጊዜ ከ38 ሺህ በላይ የዶሮ ጫጩቶችን መፈልፈል ያስችላል፡፡

በሰአዳ ጌታቸው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version