Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ቼልሲ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ድል የቀናቸው ሲሆን፥ ሲሆን በአንዱ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ በሊጉ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሜዳው ኢትሃድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ ከዌስትሃም ጋር ያደረጋቸውን ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች በማሸነፍ የበላይነት ያለው ሲሆን፥ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ አርሰናል እስኪጫወት ድረስ ሊጉን በ37 ነጥብ መምራት ይጀምራል፡፡

ወልቭስ ከብሬንትፎርድ፣ ብራይተን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ቦርንማውዝ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በሊጉ ወጥ ብቃት ማሳየት የተቸገሩትን ቶትንሃም ሆትስፐር እና ሊቨርፑል የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሊቨርፑል በአራቱ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ቶትንሃም ሆትስፐር በአንዱ ድል ቀንቶታል፡፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ መሪነቱን ለማጠናከር ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኤቨርተንን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

መድፈኞቹ በሊጉ ከኤቨርተን ጋር ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን በማሸነፍ የበላይነት ያላቸው ሲሆን፥ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version