Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ – የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተከሰተው ጭጋጋማና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ አለ፡፡

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ያጋጠመው የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን ከሚቲዎሮሎጂ መረጃ መሰረት ለማወቅ ተችሏል ብሏል፡፡

በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማቋረጥ በመገደዱ የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከልና በረራዎች እስከሚቀጥሉ ድረስ መንገደኞች እንዲታገሱና ሌላ የጉዞ አማራጭ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ፥ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ደምበኞቹን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

Exit mobile version