አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ በቆየው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ 33 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች፡፡
የውድድሩ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በውድድሩ 8 ወርቅ፣ 9 የብር እና 16 የነሃስ በጥቅሉ 33 ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የ2027ቱን የወጣቶች ኦሊምፒክ እንድታዘጋጅ መመረጧ የሚታወስ ሲሆን፥ የአዘጋጅነት አርማውን ከአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በይፋ ተረክባለች፡፡
በሙባረክ ፋንታው

