Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደብረብርሃን ከተማ 14 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የደብረ ብርሀን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 14 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ቡድን በከተማዋ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው።

በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ አምራች ኢዱስትሪዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ መመልከትና እያጋጠሟቸው ያሉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ብርሃን ገ/ህይወት በወቅቱ እንዳሉት፤ በከተማዋ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 14 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል።

በከተማዋ ከ36 ሺህ በላይ የስራ ዕድል የፈጠሩ 680 ፋብሪካዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅማቸው ስራ ሲጀምሩ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version