Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል – ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል አሉ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ማጠቃለያ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ባቀረቡት ማብራሪያ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዕቅድን ለማሳካት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ይተገበራሉ ብለዋል።

ዕቅዱ አካታች የቴክኖሎጂ እድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ ዕቅዱን እውን ለማድረግ ዘርፉን ማሸጋገር የሚችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንደሚተገበሩ ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂዎቹ ዲጂታል ኢኮኖሚውን ማስተካከል የሚችሉ፣ የመንግስት አስተዳደር ስራዎችን የሚያዘምኑ እና አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና አፍሪካ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ተከታይ እንጂ ፈጣሪ አልነበሩም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤት ማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ሉዓላዊነት ሮቦቲክስ በስትራቴጂው ዕቅድ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ ቴክኖሎጂዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ቴክኖሎጂዎቹ በፋይናንስ፣ ጤና፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳርን ማስፋት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው፤ ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል ብለዋል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version