አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ በክልሉ ባለፉት አራት ዓመታት ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ በአሲዳማነት የተጠቃ መሬት ታክሞ ወደ ምርታማነት ገብቷል አለ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አሸናፊ ክንፉ እንዳሉት፤ በአሲዳማነት የተጠቃ መሬትን በኖራ በማከም ለምነታቸውን የመመለስ ስራ ተጠናክሯል።
በክልሉ ሊታረስ ከሚችለው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ ከ800 ሺህ ሄክታሩ በአሲዳማነት ተጠቅቷል ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ከምርት የወጡ መሬቶች ዳግም ወደ ምርት እንዲመለሱ የተሰራው ስራ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ ጀምሯል ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ አሲዳማ መሬትን ለማከም ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተጀመረው የተቀናጀ ተግባር ውጤት እያመጣ ስለመሆኑ አንስተዋል።
የመሬት አሲዳማነትን ለማከም ለሚውለው ኖራ የሚሆን ግብዓት በክልሉ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በቀጣይ የኖራ ማምረቻ ፋብሪካዎችን በመትከል ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በፍሬው አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

