Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ዘጠነኛ ሳምንት ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ዘጠነኛ ሳምንት የድምጻውያን ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡

በርካታ ባለተሰጥኦ ድምጻውያን ብርቱ ፉክክር የሚያሳዩበት የፋና ላምሮት ውድድር በመጪው ቅዳሜም ለሁለት ወራት በ2 ምድብ ተከፍለው ሲወዳደሩ የቆዩት ስምንት ምርጦች ይገናኙበታል።

በቅዳሜው ውድድር ዳዊት ኪ/ማሪያም፣ ታፈረ አሰፋ፣ አሮን ሀይሉ፣ አቤል ጌትነት፣ የአብስራ ዘውዱ፣ በሱፈቃድ ገዛኸኝ፣ ግዛቸው አማረ እና ፍሬው ሙሉጌታ በቀጥታ ሥርጭት ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት የሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል።

ይህ ደማቅ ውድድር በቀጥታ ሥርጭት ቅዳሜ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በፋና በሁለቱም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ዩትዩብ፣ ፌስቡክና የቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በwww.fanamc.com ለአድማጭ ተመልካቾች በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል፡፡

አድማጭ ተመልካቾች በውድድሩ እየተዝናኑ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የዕለቱን የተወዳዳሪዎች መለያ ኮድ በመላክ ድምጽ መስጠት ይችላሉ፡፡

በለምለም ዮሐንስ

Exit mobile version