Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቆላማ አከባቢ ያለን ሰፊ የእርሻ መሬት ለማልማት በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አዲሱ አረጋ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በሀገሪቱ ቆላማ አካባቢ ያለን ሰፊ የእርሻ መሬት ለማልማት በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ፡፡

አቶ አዲሱ አረጋ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን በረዓኖ እና ጎዴ ወረዳ የተለያዩ የግብርና ልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት÷ በክልሉ 10 ሚሊየን ሔክታር የሚጠጋ መሬት ለእርሻ የሚውል መሆኑንና ከዚህ ውስጥም 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታሩ በመስኖ የሚለማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በለውጡ ዓመታት ለመስኖ ልማት ሥራ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰው ÷ አሁን ላይ በክልሉ ሸበሌ ወንዝን ለዚህ ዓላማ በስፋት የማዋል ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ማሕበረሰቡ ምርትን መጠቀም ብቻ ሳይሆን በስፋት እንዲያመርት እና ተጠቃሚ እንዲሆን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በተለይም በሩዝ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ላይ በተከናወነ ሥራ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮችን ሕይወት መቀየር መቻሉን ነው ያወሱት፡፡

የሩዝ ምርትን ከውጭ ለማስገባት ከ245 ሚሊየን ዶላር በላይ ሲወጣ እንደነበር አስታውሰው÷ ተኪ ምርትን ለማሳደግ በተከናወነ ሥራ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሔክታር በሩዝ ምርት እየለማ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህም ከ80 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ያስረዱት አቶ አዲሱ ÷ ይህን የሀገር ግብ ለማሳካት የሚያስችል ጠንካራ ሥራ በሶማሌ ክልል እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በሥራ ሒደቱ ከፍተኛ የሥራ እድል መፈጠሩን ገልጸው÷ ተግባራቱ እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የተያዘውን ግብ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል፡፡

በታምራት ደለሊ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version