አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የዐፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት አራት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
አዘጋጇ ሞሮኮ ከማሊ እንዲሁም ግብፅ ከደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር በምድብ ሁለት የሚገኙት አንጎላ እና ዚምባቡዌ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በዚሁ ምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ የቻሉት ግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ ምሽት 12 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በምድብ አንድ የሚገኙት ዛምቢያ ከኮሞሮስ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ ከማሊ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

