አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ11ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቻልን ግቦች መሀመድ አበራ (2) እና በረከት ደስታ አስቆጥረዋል፡፡
አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ አህመድ ሁሴን ከመረብ አሳርፏል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ መድን እና ሲዳማ ቡና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እያደረጉት የሚገኘው ጨዋታ 1 አቻ በሆነ ውጤት ቀጥሏል፡፡
ለኢትዮጵያ መድን ረመዳን የሱፍ እንዲሁም ለሲዳማ ቡና ደግሞ ብርሀኑ በቀለ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

