Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አንጎላ እና ዚምባቡዌ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 9 ሰዓት የተገናኙት አንጎላ እና ዚምባቡዌ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ጄልሰን ዳላ ለአንጎላ እንዲሁም ኖሌጅ ሙሶና ለዚምባቡዌ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጨዋታው ቀጥሎ ሲካሄድ ግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ ምሽት 12 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 በምድብ አንድ የሚገኙት ዛምቢያ ከኮሞሮስ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አዘጋጇ ሞሮኮ ከማሊ ጋር ይጫወታሉ።

Exit mobile version