አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው በወረዳው ብርብራ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሞጣ ወደ ግንደ ወይን የሚጓዝ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ዶልፊን) በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡
በአደጋውም የ3 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ሌሎች በአደጋው ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በሞጣ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከጎንቻ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

