Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመነጋገር ለሀገር የሚጠቅሙ ሃሳቦች ወደ ፊት ይመጣሉ – አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለዩ ሃሳቦች ሲመጡ ትኩረት መደረግ ያለበት በሃሳቡ ላይ እንጂ በሃሳብ አምጭው ማንነት ላይ መሆን የለበትም አሉ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፡፡

ሀገር የቤተሰብ ስብስብ ነው፤ በቤተሰብ ውስጥ ደግሞ ልዩነት ይኖራል ያሉት አረጋ (ዶ/ር)÷ በዚህም የሃሳብ ልዩነቶች እንደሚኖሩ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ አንስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን ከሚያለያዩን ይልቅ ያጣመሩን ጉዳዮች በርካታ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

በሚስተዋሉ ጥቃቅን ችግሮች ከመጨናነቅ ይልቅ ለሺህ ዘመናት የተገነባው አንድነታችን፣ እርስ በርስ ያስተሳሰረን ባህላችን ጠንካራ መሆኑን መረዳት አለብን ብለዋል፡፡

አብሮነት እና አንድነት በኢትዮጵያ እንዳለ ማመን እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም በመነጋገር እና በመግባባት መፍታት ይጠበቃል ያሉት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)÷ በዚህ የመነጋገር ሂደት ውስጥ ለሀገር የሚጠቅሙ ሃሳቦች ወደ ፊት እንደሚመጡ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያውያን አብሮነት ሁልጊዜም እንደሚኖር ገልጸው÷ አንድነቱም በፖለቲካዊ ነፋስ በቀላሉ የሚፈረካከስ አይደለም ብለዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇
https://www.youtube.com/watch?v=FIaZr85vZx8

Exit mobile version