አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዘመናዊነቱን በጠበቀ መልክ እድገቱን አስቀጥሏል አሉ የመከላከያ ሠራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን።
የመከላከያ ሠራዊት የሠሜን ምስራቅ ዕዝ የቡርቃ ማሠልጠኛ ማዕከል መሠረታዊ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ወደ ዕዙ ለተቀላቀሉ አባላት ተጨማሪ አቅም የሚሆንና ብቃት የሚያሳድግ ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።
ጀኔራል ይመር መኮነን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዘርፈ ብዙ ተልዕኮዎችን በመውሰድ በቀጥታ እየሰራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ጠላቶች ሀገራዊ ጥቅምን ለማሳጣት በየወቅቱ በውጭም በውስጥም ትንኮሳ እንደሚያደርጉ ገልጸው÷ ይህንንም በመረዳት ሠራዊታችን የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ዘመናዊነቱን በጠበቀ መልኩ እድገቱን ጠብቆ ቀጥሏል ብለዋል።
የሠሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል አሰፋ ቸኮል ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሀገሪቱን ባህልና እሴት በማክበርና በማስከበር የሕዝብን ሰላም እና የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር አደራችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።
ተመራቂዎቹ ከነባር የዕዙ አባላት አቅማቸውን ሊያጠናክር የሚችል ሁለንተናዊ ስልጠና መውሰዳቸው ለሠራዊቱ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል።
በስልጠናው ጠንካራ አካላዊና ሥነልቦናዊ አቅምን በማሳደግ በጠላት ላይ አሸናፊነትን የሚያጎናጽፍ ሁለገብ ወታደራዊ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል ያሉት ደግሞ የሰሜን ምስራቅ እዝ የቡርቃ ማሠልጠኛ ማእከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ ስዩም ናቸው።
የአካላዊና አዕምሯዊ ብቃታቸውን የሚያሳድግ ተግባራዊ ስልጠና በልምምድ እና በቴክኒካል ሙከራ ጭምር እንዲያገኙ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የተለያዩ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እና የክልሎች የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአለባቸው አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

