Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ ለሕዝብ ሁለገብ አገልግሎት የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማምሻውን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ የመሪ ሎቄ አካባቢ ለሕዝብ ሁለገብ አገልግሎት የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ይህ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳይ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ፣ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ ለውድድር፣ ለዕረፍትና ለህጻናት መጫወቻነት ምቹ ሆነው የተገነቡ ናቸው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ በ10 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን ገልጸው፤ ለከተማችን ጽዳትና ውበት ተጨማሪ አቅም የፈጠረ ድንቅ ስራ ነው ሲሉም አመላክተዋል።

በውስጡ ያካተታቸውም፦
• ሁለት ዘመናዊ የአዋቂዎችና የህፃናት እግር ኳስ ሜዳዎች።
• የቅርጫት ኳስ፣ የቴኒስና የመረብ ኳስን አጣምሮ የያዙ ሁለገብ ሜዳዎች።

ለተፈጥሮ አድናቂዎች፦
• በተፈጥሮ ድንጋይ ያጌጠ አስደናቂ ፋውንቴንና ፕላዛ፣
• ⁠በማራኪ አበባዎች ያማረ አረንጓዴ ስፍራ፣

• ⁠ጸጥ ያሉ የማንበቢያ ቦታዎች እና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች።
• ሙሉ የመጫወቻ ቁሳቁስ የተገጠመለት የህጻናት ማልሚያ (ECD)።

• ዘመናዊ ካፌቴሪዎች።
• ከ400 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ።
• ለኤሌክትሪክ መኪኖች የኃይል መሙያ (EV Charger)።

• የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች
• አካባቢውን በስዕልና በቀለም ያስጌጡ የጥበብ ስራዎች ወዘተ ተካትተውበታል።

ይህ ፕሮጀክት ያረፈበት መሬት፣ በደላሎች እጅ የነበሩ 23 ህገ-ወጥ ካርታዎችን በማምከን መሬቱ መልሶ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል የተደረገበት ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ የአካባቢው ነዋሪዎችና ወጣቶች በስራ ዕድል ተደራጅተው የፕሮጀክቱ ዋነኛ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓልም ነው ያሉት።

መዲናችንን በየዕለቱ እየለወጥን፣ ቃላችንን በተግባር እያረጋገጥን እንቀጥላለን ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version