Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል መንግሥት ለጤና መድሕን አገልግሎት 845 ሚሊየን ብር ድጎማ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል መንግሥት ለጤና መድሕን አገልግሎት 845 ሚሊየን ብር ድጎማ አድርጓል አለ የክልሉ ጤና ቢሮ።

የቢሮው የጽ/ቤት ኃላፊ ክሽን ወልዴ በማሕበረሰብ ጤና መድሕን አባላት የሚነሳውን የመድኃኒት አቅርቦት ቅሬታ ለመፍታት የክልሉ መንግሥት 845 ሚሊየን ብር ድጎማ ማድረጉን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

የማሕበረሰብ አቀፍ ጤና መድሕን አባላት በጤና ተቋማት በልዩ መስኮት አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ገልጸው÷ የጤና ተቋማት የውስጥ ገቢያቸውን ለመድኃኒት ግዥ እንዲያውሉም አቅጣጫ ተሠጥቷል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ ከ12 ሚሊየን በላይ ዜጎች በጤና መድሕን አገልግሎት ህክምና ማግኘታቸውን ጠቁመው÷ ለዚህም ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ መደረጉን አመላክተዋል።

ህክምና ካገኙት ውስጥም 51 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በተያዘው በጀት ዓመት የአባላት ምዝገባና እድሳት ከታሕሣሥ 1 ጀምሮ በማከናወን 4 ነጥብ 5 ሚሊየን አባላትን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ እስካሁን 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎችን መመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

በበላይነህ ዘላለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version