Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት አራት የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በምድብ አንድ አዘጋጇ ሞሮኮ ከከዛምቢያ እንዲሁም ኮሞሮስ ከማሊ ምሽት 4 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ምድቡን ሞሮኮ በአራት ነጥብ እየመራች ሲሆን ማሊ እና ዛምቢያ በሁለት ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ኮሞሮስ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር በምድብ ሁለት ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቷን ያረጋገጠችው ግብጽ ከአንጎላ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ከዚምባቡዌ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምድቡን ግብጽ ስድስት ነጥብ በመያዝ እየመራች ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ላይ ተቀምጣለች።

አንጎላ እና ዚምባቡዌ አንድ አንድ ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

Exit mobile version