አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ኢራቅ ኤርቢል ግዛት በጣለው ከባድ በረዶ የነፍስ አድን ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
የግዛቷ ሶራን ወረዳ ሲቪል መከላከያ ዳይሬክተር ካርዋን ሚራውዴሊ እንዳሉት÷ በጣለው ከባድ በረዶ የተነሳ 19 ሰዎች ያሉበት ሁኔታና ቦታ ሊታወቅ ባለመቻሉ የነፍስ አድን ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።
ከጠፉት 19 ሰዎች መካከል 11 ሰዎች ማንነታቸው በመታወቁ ከመኖሪያቸው አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች በነፍስ አድን ቡድኖች እየተፈለጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የቀሩ ስምንት ሰዎች ደግሞ በወቅቱ በሲዴካን ድንበር አቅራቢያ ከብቶችን ሲጠብቁ እንደነበርና እስካሁን ስለእነርሱ ምንም አይነት መረጃ አለመገኘቱን ጠቅሰዋል።
በትራፊክ ፖሊሶች እና በመንገድ ጥገና ባለሙያዎች የተደገፉ ስድስት የነፍስ አድን ቡድኖች በሶራን እና ሲዳና ወረዳዎች ላይ ተሰማርተው በደርዘን የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎችን በማዳንና የተዘጉ መንገዶችን በማጽዳት ላይ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።
እስካሁን በተደረገው የነፍስ አድን ስራ አራት ሰዎች ከበረዶ ማትረፍ መቻሉንም ጠቅሰዋል።
በኢራቅ ኩርዲስታን ክልል ለበርካታ ቀናት ከባድ በረዶና ቅዝቃዜ በመከሰቱ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅና በኤርቢል ግዛት ደግሞ የተወሰኑ ተራራማ መንገዶች በበረዶ ምክንያት መዘጋታቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

