Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የምርምር ሥራዎችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የምርምር ስራዎችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

ማዕከሉ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ በምርምር ያላመደውን “መልካም” የተባለ የማሽላ ዝርያ ለአርሶ አደሮችና ለግብርና ባለሙያዎች አስተዋውቋል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ደረጀ ቱሉ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የምርምር ማዕከሉ ለ3 ዓመታት ምርምር ሲያደርግበት የቆየው “መልካም” የማሽላ ዝርያ ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ ነው፡፡

የማሽላ ዝርያው ከነባሩ የአካባቢ ዝርያ በምርት የተሻለና ድርቅን የመቋቋም አቅም እንዳለው ገልጸው÷ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡

የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚታወቅበት የቅመማ ቅመምና ቡና ምርምር ስራ ባሻገር በሰብልና በሥራ ስር ሰብሎች የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የምርምር ስራዎችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በማዕከሉ የሆርቲካልቸር ተመራማሪና የሰብል ምርምር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ሻሚል አሎ በበኩላቸው÷ “መልካም” የተሰኘው የማሽላ ዝርያ በሄክታር ከ40 እስከ 45 ኩንታል ምርት የሚሰጥ በመሆኑ ከነባሩ ዝርያ በእጥፍ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በዚህም ከፍተኛ ምርት የሚሰጠውን ዝርያ ለአርሶ አደሮች በስፋት ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version