Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር ሃብት 5 ነጥብ 22 ቢሊየን ብር ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ከታክስ በፊት ከ616 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገብሁ አለ፡፡

የኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዳኛቸው መሐሪ እንዳለት÷ በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ሀብት 5 ነጥብ 22 ቢሊየን ደርሷል፡፡

አክሲዮን ማኅበሩ ያስመዘገበው ትርፍ ከታክስ በፊት 616 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር መሆኑን ገልጸው÷ ከቀዳሚው ዓመት የ45.3 በመቶ ወይም የ192.3 ሚሊዮ ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡

ኩባንያው ከሀገር ውስጥና ከውጭ በጠቅላላና በረጅም ጊዜ መድን ዘርፍ 2 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር አጠቃላይ የጠለፋ መድን ገቢ ማገኘቱን አመልክተዋል፡፡

ኩባንያው ባለፈው የሒሳብ ዓመት 406 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የኢንቨስትመንት ገቢ ማስመዝገቡን ነው ያስረዱት፡፡

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር ሃብት 5 ነጥብ 22 ቢሊየን ብር መድረሱንም ሊቀመንበሩ አመልክተዋል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ ከተገኘው ጠቅላላ ገቢ ውስጥ አምስት በመቶ የሚሆነው ከኢትዮጵያ ውጪ ለተሰጡ የጠለፋ መድን ሽፋኖ በውጭ ምንዛሪ ነው፡፡

ኩባንያው ከኢትዮጵያ ውጭ በመንቀሳቀስም የሚታወቅ መሆኑን፣ በአምስት ዓመት ዕቅዱ መጨረሻ ላይ ከኩባንያው ጠቅ ገቢ አምስት በመቶው ለውጭ ኩባንያዎች ከሚሰጠው የመድን ሽፋን የሚገኝ መሆን አለበት የሚል እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር ታሕሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version